ምስክሮቼ ትሆናላችሁ

ኢያሱ ፈረንጅ

ዶ/ር ኢያሱ ፈረንጅ

ዶ/ር ኢያሱ ፈረንጅ በወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ግዙፍ በሆነቿ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን (የኢ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ) ፣ የቤተክርስቲያን ተከላ ዋና ኃላፊ ናቸው። በኢትዮጵያ ቃል ሕይወት ከ8, 000 በላይ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት አሉ፤ ይህም 8 ሚሊዮን አባላትን ይወክላል። ዶ/ር ኢያሱ ፈረንጅ በዶ/ር ጌሪ ብሬሽርስ ሥር ከዌስተርን ሴሚናሪዩም በሚሲዮሎጂይ ዶክትሬታቸውን ተቀብለዋል።

ዶክቴር ኢያሱ ፈረንጅ፥ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ በምለው መጽሐፋቸው ላይ በወንጌል ሥርጭት እና በወንጌላዊነት፣ የአውዳዊነትን አገልግሎት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ እና ምዕመናን በወንጌል ምስክርነት ማሳተፍ በሚል አንኳር አንኳር ርዕሶችን ዙሪያ ላይ በጥልቀት እና በዝርዝር አብራሪተዋል። ይህ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ የሚለው መጽሐፋቸው ስነ መለኮታዊ፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊና በከፍተኛ ሁኔታ ተግባራዊ በሆነ መልኩ የቀረበ ነው። መጽሐፉ ከጽንሰ ሃሳብ ባለፈ በተግባር የተፈተኑ ተግባራዊ መሪሆዎችን በድንቅ ሁኔታ ይዳስሳል። በአጠቃላይ ስለ ወንጌላዊና ስለ የወንጌል ሰባኪነት ሥራ በግልጽ ተብራሪቷል። ምናልባትም ያለማጋነን በአገራችን እስከ አሁን በወንጌል ሥርጭት ዙሪያ ተጽፈው ካነበብኳቸው መጽሐፍቶች በእጅጉ የተለየ በመሆኑ ፈር ቀዳጅ ነው።

ይህ መጽሐፍ በስነ መለኮት ትምህርት ቤቾች እንዴ መማሪያ መጽሐፍ ተደርጎ ቢወሰድ እጅግ የተሻለ ነው። በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ክርስቲያኖች  ሁሉ ይህን መጽሐፍ ገዝተው ማንበብ አለባቸው ። በተለይም የወንጌል ልብ ያላቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ ሚሲዮናዊያን፣ ወንጌላዊያን፣ መጋቢዎችና አስተማሪዎች ይህን መጽሐፍ እንዲያነቡት እመክራለሁኝ። 

በአሜሪካ የምትገኙ ውድ የኢትዮጵያ መጋቢዎች፣

የዚህን መጽሐፍ ኮፒ እንደ ሥጦታ በነጻ ላበረክትላችሁ እወዳለሁ። ምስክሮቼ ትሆናላችሁ የሚለውን የአማርኛ መጽሐፍ ትርጉም የኢየሱስን መልካሙን ዜና ለማሰራጨት እንደምትገለገሉበት ተስፋ አደርጋለሁ። ከብዙ ፍቅር እና የጸሎት ድጋፍ ጋር።

— ሰተን ተርነር

ነጻ ኮፒ ይጠይቁ


ይህን ቅጽ ስታስገቡ “ምስክሮቼ ትሆናላችሁ” የሚለውን መጽሐፍ ኮፒ መጠየቃችሁ በመሆኑ ቤተክርስቲያናችሁ እንድታገኝ ታደርጋላችሁ እናም ያስገባችሁት የቱም መረጃ
InvestYourGifts.com በሚለው ወይም ተጓዳኝ በሆኑ ድህረ ገጾች ላይ ይገለጻል።

 

አባት እግዚአብሄር ሆይ፣ አንተን የሚፈራ መሪ ለቤተክርስቲያናችን ስለሰጠሄን በኢየሱስ ስም አመሰግንሃለሁ። ከዚህ ቀደም ለእስራኤላዊያን አሁን ደግሞ ለቤተክርስቲያን አንተ ለሕዝብህ ሁሌም ታስባለህ።

ጌታ ሆይ፣ ፓስተር በአገልግሎቱ ፍሬያማ ባሪያ እንዲሆን እንድትመራው እና አብሮነትህ ከእርሱ ጋር እንዲሆን እጸልያለሁ።

ጌታ ሆይ፣ ከዲያብሎስ ወጥመድ ሕይወቱን እና ጤናውን እንድትጠብቅ እጸልያለሁ። ጌታ ሆይ፣ ለቤተሰቡም፣ ጤናቸውን እንድትጠብቅ፣ ሰላማቸውን እንድትጠብቅ፣ እጸልያለሁ። ጌታ ሆይ፣ የቤተሰቡን አንድነት ከሚያጠፋ ከየቱም አይነት ከዲያብሎስ ጥቃት እንድትጠብቃቸው እጸልያለሁ። ጌታ ሆይ፣ የሚያገለግላቸውም ምእመናን በመንፈሳዊዉም በሥጋዊዉም ሕይወት እንዲጠበቁ እጸልያለሁ። ጌታ ሆይ፣ ከተለያዩ ፈተናዎች እንድትጠብቃቸውም እጸልያለሁ።

ጌታ ሆይ፣ በማቴዎስ ምዕራፍ 28፥18-20 መሠረት ፓስተር ላላመኑ ሰዎች በሰፈሩና በአከባቢው የአንተ ምስክር እንዲሆንና ደቀ መዝሙር እንዲያፈራ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንድትሞላው እለምንሃለሁ።

ጌታ ሆይ፣ ይህን ሁሉ ለክብርህ እና ለመንግስትህ መስፋፋት ስለምታደርግ አመሰግንሃለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን።